ስለ እኛ

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያን ካውንስል ተልዕኮ፡-

ቤተ እምነቶች፤ ኅብረቶች፤ ሚኒስትሪዎች እና ሌሎች ለተመሳሳይ ዓላማ የተቋቋሙ አካላት የታላቁ ተልዕኮን ግብ ማሳካት ይችሉ ዘንድ አስፈሊጊውን ድጋፍና እገዛ ማድረግ፤ የወንጌል አማኞችን የጋራ ችግሮች፤ ጥያቄዎችና በየወቅቱ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶች የጋራ ድምጽ ሆኖ ማገልገል ፤ የአገሪቱ ሰሊም እንዲይናጋ ለመከላከል፤ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ሲያጋጥሙም የካውንስሉን አባላት በማስተባበር አዎንታዊ አስተዋጽዖ ማበርከት ፤ የአባላቱን የእርስ በርስ ግንኙነት ማጠናከርና መልካም ምሳሌነታቸው ጎልቶ እንዲታይ መደገፍ ነው፡፡


የካውንስሉ ዓላማዎች

 • ቤተ እምነቶች፤ ኅብረቶች፤ ሚኒስትሪዎች እና ሌሎች ለተመሳሳይ ዓላማ የተቋቋሙ አካላት የታላቁ ተልዕኮን ግብ ማሳካት ይችሉ ዘንድ አስፈሊጊውን ድጋፍ ማድረግ፤
 • ካውንስሉ በተቋቋመባቸው ዓላማዎች ረገድ የወንጌል አማኞች እምነት ተከታዮች የጋራ ድምጽ ሆኖ ማገልገል፤
 • በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል ችግር ሲፈጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ችግሩ እንዱፈታ፤ ሰላምና መቀባበል እንዲሰፍን አስተዋፅዖ ማድረግ፤
 • በሕገ መንግሥቱና አግባብነት ባላቸው ሌሎች ሕጎች የተከበሩ የእምነትና የሐይማኖት ነጻነት መብቶች እንዱረጋገጡ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ እንዲኖር ምርምር ማድረግ፤ የምርምሩን ውጤት ለሚመለከተው የመንግሥት አካሌ ማቅረብና ተግባራዊነቱን መከታተል፤
 • በሕግ የተከበሩ የእምነትና የሐይማኖት ነጻነት መብቶች በልማዳዊ አሠራር እንዲይሻሩ እና እንዲይሸራረፉ በሥራ ላይ ያለ ሕጎች ለሁለም የሐይማኖት ተቋማት በእኩልነት ተፈፃሚ እንዲሆኑ መሥራት፤
 • ከሌሎች የሐይማኖት ተቋማት ጋር በመሆን ኅብረተሰቡ በሐይማኖት፣ በዘር ወይም በሌላ ማኅበራዊ መለያ ሳይለያይ ተከባብሮና ተቀባብሎ እንዲኖር መሥራትና ማስተማር፤
 • ቤተ እምነቶች፤ ኅብረቶች፤ ሚኒስትሪዎች እና ላሎች ለተመሳሳይ ዓሊማ የተቋቋሙ አካሊት በተለያየ መንገድ ጥቃት ሲደርስባቸው አጥፉዎች እንዱጠየቁ ከሚመለከተው የመንግሥት አካሊት ጋር በመሆን ተገቢውን ክትትል ማድረግ፤
 • ቤተ እምነቶች፤ ኅብረቶች፤ ሚኒስትሪዎች እና ሌልች ለተመሳሳይ ዓሊማ የተቋቋሙ አካላት በመካከላቸው አለመግባባት ሲፈጠር አለመግባባቱ ክርስትያናዊ እና ሰሊማዊ በሆነ መንገድ የሚፈታበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤
 • የአባላቱን አቅም በሥልጠና መገንባት፤
 • የተፈጥሮ ወይም ሰው ሠራሽ አደጋ ሲያጋጥም አባላቱ አደጋውን የማቃለል ሥራ እንዱሠሩ ማስተባበር፤ ድጋፍ መስጠት፤
 • የአብያተ ክርስትያናት ሕልውናን የሚፈታተን ጉዳይ ሲያጋጥም መከታተል፤ የመፌትሔ አቅጣጫ ማስቀመጥ፤
 • አዲዲስ ቤተ-እምነቶችን በተለያየ መንገድ መደገፍ ፣ ማቃናትና መርዳት፤
 • በሕግ መሠረት የወንጌሌ አማኞች የሐይማኖት፣ የማኅበራዊ፣ የልማትና የትምህርት ተቋማትን መመዝገብ፤ ድጋፍ ማድረግና መከታተል፡፡

የካውንስሉ መርሆዎች

 • የሥርዓትና የመርሆዎች መሠረትና መነሻ መጽሐፍ ቅደስ ነው፡፡
 • የአባላት የውስጥ አሠራር፤ ሕጋዊ ሰውነት ተቋማዊ ነጻነት፤ የሐይማኖት ቀኖና ወይም አስተምህሮ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
 • ውሳኔዎች በተቻለ መጠን በስምምነትና በመግባባት እንዱያልፉ ይደረጋል፡፡
 • የአመራር ዘይቤ አገልጋይ መሪነት ነው፡፡
 • አባላት በትብብር፤ በቅንጅትና በተሳትፍ ያገለግላሉ፤ የካውንስሉ አባላት ሁሉም የሚቀበለትን አስተሳሰብና አሠራር ይከተላሉ፡፡
 • ካውንስሉ በእግዙአብሔር ቃል ላይ በመመሥረት የካውንስሉን አባላት አቅም ማጎልበት፤ አሠራራቸውን ማዘመን፤ ማሰልጠንና የጋራ ችግሮቻቸውንም በመፍታት ቅድሚያ ይሰጣል፡፡

የጋራ ዕሴቶች

 • የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ
 • ቅድስና
 • ትብብር፤ ስምምነት፤ መግባባት
 • ቀና አስተሳሰብ (ቅንነት)
 • ተሐድሶና ለውጥ ፤
 • ሚዚናዊነት ፤ ጽድቅና ፍትህ
 • መከባበር
 • የመንፈስ አንድነት
 • ሁሌ ጊዜ መማር ፤ ማስተዋል ፤ ጥበብና እውነተኛ መንፈሳዊነትን መጨመር ፤
 • አገልጋይ መሪነት፤
 • ግሌፅነት፤ ተጠያቂነት፤ ኃላፊነት፤ አሳታፊነት፤ አካታችነት
 • እግዚአብሄርንና ሰውን መውደድ