የምዝገባና አስተዳደር

የምዝገባና አስተዳደር መምሪያ

  1. በሕግ መሠረት የወንጌል አማኞችን የሐይማኖትና የትምህርት ተቋማትን ይመዝገባል፤ ድጋፍ ያደርጋል ይከታተላል፡፡
  2. ለምዝገባ እና ለድጋፍ የሚረዱ መመሪያዎችን፣ ፖሊሲዎችን፣ ማኑዋሎችንና ቅጾችን ያዘጋጃል፡፡
  3. የሐይማኖትና የትምህርት ተቋማት አቅማቸውን የሚያጎለብቱበትንና አሰራራቸውን የሚያዘምኑበትን ሁኔታዎች ጥናት ያደርጋል፡፡
  4. የወንጌል አማኞችን የልማትና ማኅበራዊ ተቋማትን በሕግ መሠረት ይመዘግባል፤ ይከታተላል ድጋፍ ያደርጋል ፡፡
  5. የልማት ማኅበራዊ ተቋማት አቅማቸውን የሚያጎለብቱበትንና የሚያዘምኑበትን ሁኔታዎች ያጠናል
  6. የልማትና ማኅበራዊ ተቋማት ሥራቸውን በግልጸኝነትና በተጠያቂነት መርህ መሠረት የሚሠሩ ለመሆኑ ይከታተላል፤ ያረጋግጣል፡፡
  7. የልማትና የማኅበራዊ ተቋማቱን ዓመታዊ የሥራ የበጀት እቅድና የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ይቀበላል፤
  8. የልማትና ማኅበራዊ ተቋማቱ እርስ በእርሳቸው እንዲደጋገፉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡
  9. የልማትና ማኅበራዊ ተቋማቱ ድጋፍ መድረክ /ሕብረት/ እንዲፈጥሩ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡