ምዝገባ

 

የአዲስ ቤተ እምነት የምዝገባ መስፈርት

 • ቤተ እምነት እንዲመሰረት ውሣኔ ያሳለፉበትን ቃለ ጉባኤ
 • ስያሜና ዓርማ የተመረጠበትን ቃለ ጉባኤ
 • የቤተ እምነት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ፤ ቦርድ ወይም መሪዎች የተመረጡበትንና ኃላፊነታቸውን የሚገልጽ ቃለ ጉባኤ
 • በመሥራቾች/ጠቅላላ ጉባኤ የተፈረመ የመተዳደሪያ ደንብ ፤
 • የ100 ሰዎች የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ አድራሻና ስልክ ቁጥራቸው ፊርማ ያለበት በፎርማቱ መሠረት፡፡
 • በካውንስሉ ለመመዝገብ ሽኚ ደብዳቤ

የአዲስ ሚኒስትሪ የምዝገባ መስፈርት

 • ሚኒስትሪው እንደትመሰረት ውሣኔ ያሳለፉበትን ቃለ ጉባኤ
 • ስያሜና ዓርማ የተመረጠበትን ቃለ ጉባኤ
 • የሚኒስትሪው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ፤ ቦርድ ወይም መሪዎች የተመረጡበትንና ኃላፊነታቸውን የሚገልጽ ቃለ ጉባኤ
 • በመሥራቾች/ጠቅላላ ጉባኤ የተፈረመ የመተዳደሪያ ደንብ ፤
 • የ20 ሰዎች የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ አድራሻና ስልክ ቁጥራቸው ፊርማ ያለበት በፎርማቱ መሠረት፡፡
 • በካውንስሉ ለመመዝገብ ሽኚ ደብዳቤ

የዳግም ምዝገባ መስፈርት (ፈቃድ ያላቸው) የሚኒስትሪዎች

 • ከሚመለከተው መዝጋቢ አካል የተሰጠውን የፍቃድ የምስክር ወረቀትና መሸኛ ደብዳቤውን፤
 • ስለ ተቋሙ አገልግሎትና እንቅስቃሴ የሚገልፅ ከአምስት ገጽ የማይበልጥ ሪፖርት
 • ፍቃድ በሰጠው አካል የጸደቀ መተዳደሪያ ደንብን ቅጂ፤
 • ቤተ እምነቱ /የሚኒስትሪው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ /ቦርድ/መሪዎች የተመረጡበትን ቃለ ጉባኤ፡፡
 • በካውንስሉ ለመመዝገብ ሽኚ ደብዳቤ

የመተዳደሪያ ደንብ ይዘት

  ( - 19 አንቀፆች ያሉት ... ማውጫ ሊኖረው ይገባል ... የተጠረዘ ... ብዛት = 2)
 • 1. መግቢያ
 • 2. ስያሜ
 • (ስያሜ በእንግሊዘኛ ሲፃፍ ቀጥታ በአማርኛ- እንግሊዘኛ ይፃፋል እንጂ ስያሜ አይተረጎምም)
  ብርሃን=BIRHAN ወይም ላይት=LIGHT
 • 3. የዋና ጽ/ቤቱ አድራሻ
 • 4. አርማ (ምስሉ እዚያው ጋር መግባት አለበት )
 • 5. የእምነት አቋም
 • 6. ዓላማና ተልዕኮ ፤ እሴቶች
 • 7. የበጀት ምንጭ
 • 8. አስተዳደራዊ መዋቅር
 • 9. የውሳኔ ሰጪ አካላት የጠቅላላ ጉባኤ ፤ የቦርድ ወይም የስራ አስፈጻሚ ፤ ተግባርና ሃላፊነት
 • 10. የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓት
 • 11. የንብረት አስተዳደር ሥርዓት
 • 12. የምርጫ ስነስርዓት
 • 13. የበጀት ዓመት
 • 14. ስለ ግጭት አፈታት
 • 15. መልካም ክርስቲያናዊ ተግባራት
 • 16. ደንቦችና መመሪያዎች
 • 17. የመተዳደሪያ ደንብ የሚሻሻልበት ስርዓት
 • 18. የመተዳደሪያ ደንቡ ተፈጻሚነት
 • 19. መተዳደሪያ ደንቡ ስለሚጸናበትና ተግባራዊ ስለሚሆንበት ጊዜ
  (በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አማኞች ህብረት ካውንስል ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ይህ መተዳደሪያ ደንብ የፀና ይሆናል፡፡)

 

ካውንስሉ የሚከተለት የአባላነት ዓይነቶች ይኖሩታል፡-

 1. መደበኛ
 2. ተባባሪ
 3. በውጪ ሃገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወይም ትውለደ ኢትዮጵያውያን የወንጌል አማኞች በሚገኙበት አገር ወይም አህጉር ተደራጅተው የሚመሰርቱት ህብረት
 4. የክብር አባላት

የካውንስሉ መደበኛ አባላት፡-

 • የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ፣
 • የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን፣
 • የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስትያናት ኅብረት፣
 • የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተ ክርስትያናት ኅብረት፣
 • የኢትዮጵያ ፔንቴኮስታል አብያተ ክርስትያናት ኅብረት፣
 • የኢትዮጵያ የፍቅር ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስትያናት ኅብረት ናቸው፡፡
 • የካውንስሉን የሥነ-ምግባር ደንብና ሌሎች የካውንስሉ ደንቦችና መመሪያዎችን የሚቀበል ቤተ እምነት፤ ኅብረት ወይም ሚኒስትሪ የካውንስሉ አባል ሊሆን

  ይችላል፡፡