መንፈሳዊ ዘርፍ ዳይሬክቶሬት

መንፈሳዊ ዘርፍ ዳይሬክተር

  1. የካውንስሉ አባላት የታላቁ ተልዕኮ አገልግሎትን በተሳካ ሁኔታ እንዲፈጸሙ ለማገዝ የሚያስችል ጥናት ያደርጋል፤ ሲወሰን ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
  2. የትምህርትና የሥልጠና መርሃ ግብር ያዘጋጃል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
  3. አቅም በፈቀደ መጠን በሌሎች አባላት የማይሰሩትን ሰፋፊ መንፈሳዊ ትምህርት እና የሚሲዮን ሥራ ለመስራት የሚያስችል ጥናት ያደርጋል፤ ለውሳኔ ያቀርባል፡፡
  4. የሐይማኖትና የትምህርት ተቋማትን ለመደገፍ የሚያስችል ሥርዓት ያዘጋጃል፡፡
  5. የትምህርት ተቋማትን ደረጃ እና በተቋማቱ የሚሰጠውን የምስክር ወረቀት (የትምህርት ማስረጃ) አክሬዲቴሽን ፖሊሲ/መመሪያ/ አዘጋጅቶ ለጠቅላይ ጸሐፊው ያቀርባል፤ ሲጸድቅም አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡
  6. የትምህርት ተቋማቱን ደረጃዎችና አክሬዲቴሽን ለጠቅላይ ጸሐፊው ለውሳኔ ያቀርባል፡፡
  7. የሐይማኖትና የትምህርት ተቋማቱን መረጃ በዘመናዊ ዘዴ ያደረጃል፤ ይይዛል፡፡
  8. የትምህርት ተቋማቱን የትምህርት፣ አሰጣጥ ዘዴ ይከታተላል፤ ትምህርት የሚሰጥበትን ክፍል ወይም ሕንፃ አመቺነት ይገመግማል፤ አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፡፡
  9. በትምህርት ተቋማቱ የሚሰጠው የትምህርት ማስረጃ የሐይማኖት ተቋማት የትምህርት ተቋማት ባልሆኑ ተቋማት ዘንድ ስለሚኖረው ተቀባይነትና የአቻ ግምት አሠራር ጥናት ያደርጋል፤ ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቶም
  10. ለጠቅላይ ጸሐፊው ያቀርባል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡